‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!››

ሠላም ለእርስዎ ይሁን! ይህ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› የሰብአዊ እና የበጎ አድራጎት ሎተሪ ገጽ ነው፡፡

ይጀምሩ

0

አጠቃላይ ተጠቃሚዎች

0

አጠቃላይ አሸናፊዎች

0

አጠቃላይ ጎብኚዎች

ሎተሪው ------------ ቀን ይወጣልና እንዳያመልጥዎ!

የሎተሪው አይነት የተጀመረበት ቀን ማጠናቀቂያ ቀን ዋጋ የተሸጠ ያለበት ሁኔታ ተግብር
image
ኢትዮጵያን እናክማት የአዋቂ
2023-01-01 2024-09-06 30.00 USD
0%
Waiting For Draw ሎተሪዎን ይግዙ
image
ኢትዮጵያን እናክማት የልጆች
2023-03-01 2024-10-29 30.00 USD
0%
Running ሎተሪዎን ይግዙ
image

ዓላማው

1. ዘርፈ ብዙ ሀገራዊና ወገናዊ ጉዳቶችን በተለይ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ የሚከሰቱ ውድመቶችን ለመቅረፍ፤ መሠረታዊ ጥናቶችን ከነ ብልሀታዊ አተገባበራቸው ጋር በማሰናዳት በጽኑ የታመመችውን ኢትዮጵያን ማከም፡፡


2. በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም በተለያዩ የእውቀትና የሙያ ዘርፎች ተክነው፤በፍርሀትና በዝምታ ውስጥ ተሸፍነው ያሉ በሰብአዊነት የታነጹ ቅን የሀገር ባለውለተኞችን አፈላልጎ ወደ መድረክ በማምጣት  በሀገራዊና በወገናዊ ግጭቶቻችን ላይ ስር ነቀል የሠላም ማስፈኛ መፍትሔ መዘየድ እንዲችሉ ማድረግ፡፡ ለዚህም በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ የእውቀትና የልምድ ቅብብሎሽ እንዲኖር በማድረግ ትውልድን እየታደጉ  በሠላም እጦት የታመመችውን ኢትዮጵያችንን ማከም፡፡


ይህም፡- በአስተምሮት፣በልምድ ልውውጥ፣አዳዲስ መንገዶችን በማመላከት ..


3. በተለያዩ ግጭቶች ሳቢያ በተለያዩ ክልሎች ተፈናቃይ የሆኑና በዳስ ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖቻችን የፈረሰባቸውን ቀዬና ጎጆ ከቀድሞ በተሻለና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ  በመገንባትና የኢኮኖሚ  ድጋፍ በማድረግ  ወደቀደመ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ፡፡ ይህም፡-በመላው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር፡የገንዘብ፣ የተለያዩ የሕክምና መገልገያዎችን ፣የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን፣የተለያዩ መጽሐፍትን፣የተለያዩ አልባሳትና መጫሚያዎችን አሰባስቦ በአፋጣኝና በቀጥታ ለተጎጂዎች እንዲዳረስ ማድረግ፡፡


4. አፋጣኝ የሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ቅድሚያ በመስጠት፤ ሕጻናት፣ ሴቶች፣ አዛውንት ወገኖቻችን ከደረሰባቸው የስነ - ልቦና ቀውስ የሚላቀቁበትን የማነቃቂያ መርሀ - ግብሮችን መዘርጋት፡፡   


5. በግጭቶቹ የወደሙትንና ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተ እምነቶችን መገንባት፡፡


6. በግጭቶቹ መስዋዕት ለሆኑት ንጹሀን ኢትዮጵያውያንና ለሉአላዊነት አስከባሪው መከላከያ ሠራዊት መታሰቢያ የሚሆን የጦርነት ቀጠና በነበሩት ክልሎች በቀጣይም በሌሎች ክልሎች በኢትዮጵያ  ልዩ የሆነ 24  ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚችል   ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት›› ስም አዲስ ሆስፒታል መገንባት፡፡ 


ይተኮር፡-  የኢኮኖሚ ድጋፍ ሲባል ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ የሞቱበትንና ኑሮውን የሚያቀናበትን ከብቶቹን ስንሰጠው፤ የገበሬውንና የልጆቹን ሕመም በተዘዋዋሪ እንደማከም ነው፡፡

 

ሰብአዊ ድጋፍ ለመለገስ ከታች ያለውን መግቢያ ይጫኑ፡፡

ሰብአዊ ድጋፍ

የሎተሪው አስተማማኝነት

ሕጋዊ የመንግስት እውቅና አለው፡፡

It has legal government recognition.

አሸናፊው እንደታወቀ ሕጋዊ በሆነ መልኩ ሽልማቱን ያበረክታል፡፡

The winner will be legally awarded the prize upon notification.

ያለበትን ደረጃ በየዕለቱ በሚዲያ ይገለጻል፡፡

His status is reported daily in the media.

የ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ሎተሪ አሸናፊ ለመሆን ተግባራቶቹን በቅደም ተከተል ያከናውኑ

Complete the tasks in order to win the "Treat Ethiopia!" lottery.

1

መለያዎትን ይፍጠሩ

ይመዝገቡ የሚለውን በመጫን አባል ይሁኑ

2

ሎተሪ ይምረጡ

ኢትዮጵያን እናክማት የአዋቂ ወይም የኢትዮጵያን እናክማት የልጆች ከሚሉት አማራጮች አንዱን ይምረጡ

3

ሎተሪ ቁጥርዎን ይምረጡ

የሎተሪ ቁጥርዎን ይምረጡ

4

ያሸንፉ

ያሸንፉ/ይቅናዎት!

image

በሚገባ! ከየትኛውም ስፍራ ሆነው በተቀመጡት የክፍያ መተግበሪያዎች መግዛት ይችላሉ።

ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ ብቻ መሳተፍ ይችላል።ምክንያት "የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!"

በየጊዜው ከዕድለኞች በሚሰበሰበው ገንዘብ የወደሙ ቤቶችና ሆስፒታሎች የሚገነቡና በሁሉም ክልሎች ለሚሰሩት ስራዎች በመንግስትም በማኅበረሰቡም ክትትል ተደርጎባቸው በዜና መልክ በየቀኑ ይፋ ይደረጋሉ።

አዋቂዎች ነገ ልጆቻቸው የት እንደሚደርሱ እርግጠኛ መሆን ስለማይችሉ ካላቸው ላይ ምንም ለሌላቸው ማካፈልን ለልጆች ማስተማር እንዲችሉና የሀገር ፍቅር ከቤተሰብ እንደሚጀምር ለማስታወስ ነው።

ከ1ኛ እስከ 13ኛ ደረጃ ድረስ ባለዕድለኞች ከ25 ሚሊየን ብር ጀምሮ እስከ 5 ሚሊየን ብር በየደረጃቸው ይሸለማሉ። ይህም ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም የመጀመሪያዋ የ13 ወራት ባለፀጋ መሆኗን ለማስታወስም ጭምር ነው።

የሎተሪው አሸናፊ፡- በቅርብ ቀን!

ስለኛ

ይህ ከተለያየ ዘርፍ በአንጋፋና በወጣት ስብጥርነት የተሰባሰበው ልዩ የኃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በ ዘ ኢትዮጵያውያን ዲጂታል ኮሚኒኬሽን ኤንድ ኤቨንትስ አማካኝነት፤የኢትዮጵያ ሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ምክር ቤት፣የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፣የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት እንዲሁም በመላው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስፋ እንዲሳተፉበትና ኢትዮጵያችንን በጽናት ለማከም አንድ ዓመት ከሥድስት ወራት በላይ መሠረታዊ ጥናት በማድረግ የራሱን ቢሮ በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ምክረ ሀሳብ አሰናድቷል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት በተቋም ደረጃም፡- የራሱን ዲጂታል ስቱዲዮ፣የአይቲ ስታፍ፣የዝግጅትና ፕሮሞሽን ስታፍ፣መጠነኛ የቁሳቁሶች ማከማቻ፣ የዝግጅቶች መድረክ እንዲሁም አጠቃላይ የማኔጅመንት ቢሮ የተዘጋጀለት ሲሆን ፤ በዲጂታል ስቱዲዮ፡- ራሱን የቻለ የሚዲያ ፕላት ፎርም፣የተለያዩ የቅስቀሳ ሙዚቃዎች፣ዘጋቢ ፊልሞች፣የተለያዩ ዘውግ ያላቸው ማስታወቂያዎች እንዲሁም ይህን/እየተጠቀምንበት የምንገኘውን የሎተሪውን በይነ መረብ/ዌብሳይትን ጨምሮ የተለያዩ በርካታ ቅድመ ሥራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት ቀጣይነት ባለው ኢትዮጵያን ለማከም የሦስት ዓመት ዕቅድ መሠረት ከሦስት መቶ በላይ ሰብአዊነት የሚሰማቸውን በጎ ፈቃደኛ አባላትን አቅፎ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት እየተዘዋወረ አመርቂ ውጤት ለማምጣት ቅድመ ዝግጅቶችን በማከናወን ላይ ነን፡፡ እርሶና ቤተሰብዎም ኢትዮጵያን ለማከም ስለምታግዙን በኢትዮጵያዊነት ክብርና ፍቅር ሠላምና ክብረት ይስጥልን፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፡-

ደበበ እሸቱ /የጥበብ ሰው/ አርቲስት

image

ደበበ እሸቱ

አርቲስት

ደራርቱ ቱሉ/ክብርት ዶክተር/

image

ደራርቱ ቱሉ/ክብርት ዶክተር/

አትሌት

አቡበከር አህመድ /ኡዝታዝ/

image

አቡበከር አህመድ

/ኡዝታዝ/

የክፍያ አማራጮች

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች መጠቀም ይችላሉ