Blog Details

image

ዜና 3

www.EthiopianEnakmat.com  በይነ መረብን በመጠቀም በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንናትውልደ ኢትዮጵያውያን ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል መሪ ቃል፤በተለያዩ ምክንያቶች በጽኑ የታመመችውንኢትዮጵያችንንና ወገኖቻችንን አድሏዊ የክፋት ምኞት በማያታልለው ስብዕና እና ሰብአዊነት፤ ጉዳቱ በእጅጉ በባዛባቸው ስፍራዎች ቀዳሚ በማድረግ፤ በመላው  ኢትዮጵያ በዳስ ውስጥ ለተጠለሉ ወገኖቻችን ጎጇቸውን፣ለወደሙ ሆስፒታሎችና የትምህርት ተቋማት፣ ወ.ዘ.ተ መልሶ ለመገንባትና ወገኖቻችንን ወደቀደመ ሠላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ፣ ከደረሰባቸው ስነ ልቦናዊ ቀውስ እንዲያገግሙና በመላው ኢትዮጵያ ተጨባጭ የሠላም ግንዛቤ መፍጠሪያ መርሀ ግብሮችን መዘርጋት እንዲሁም የገንዘብ፣የሕክምና፣የመጻሕፍት፣የትምህርት ቁሳቁሶችንና  አልባሳትና መጫሚያዎችን  ማሰባሰብ ዓላማ አድርጎ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ሙያተኞች የተዘጋጀ ነው፡፡